Home
New Page
ትምህርተ ሀይማኖት:ምስጢረ ሥላሴ
ምስጢረ ሥጋዌ
ምስጢረ ጥምቀት
የላሊበላ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ምስሎች
ነገረ ማርያም
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ፃድቁ መናኝ ገብረ ክርስቶስ
የክርስቶስ ጥልቅ ፍቅር
የመንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ
መተግበሪያ (APPS)
Contact us
yilma mezmur
daniel kibret
temhirtoch
megabi eshetu
memhir zebene lemma
memhir miherete ab aseefa
mezmur
tedros yosef
our other site
live tv
read pdf files
ፃድቁ መናኝ ገብረ ክርስቶስ
ጥቅምት 14 ጻድቁ መናኝ ገብረ ክርስቶስ የእረፍቱ መታሰቢያ ቀን ነው በዚሁ ቀን አቡነ አረጋዊም የተሰወሩበት ዕለት ይታሰባል እንዲሁም ሐዋርያው ፊሊጶስ ያረፈበት ዕለት ይታሰባል፡፡ ++++++++የአባቶቻችን በረከታቸው አማላጅነታቸው ይጠብቃን+++++++++ ጻድቁ መናኝ ገብረ ክርስቶስ የንጉሱ የቴዎድዮስ ልጅ ነው፤:: ከጫጉላ ቤት ጠፍቶ መነነ፤ አባቱም ወታደሮችን ላከበት፤ ገብረ ክርስቶስ ሌት ተቀን ተጉዞ የእመቤታችንን ደብር አገኘ ተንበርክኮም እመቤቴ ወታደሮች እንዳይዙኝ መልኬን ቀይሪሊኝ አላት:: የውስጥ ሰውነቱ ተገለበጠ በቁስልም የተመታ ሆነ ደጀ ሰላሙ ላይ ምጽዋት ከሚለምኑ ድሆች ጋር ተቀመጠ የ
አባቱም ወታደሮች ደረሱበት አ ላወቁትም ምጽዋት ሰጥተውት ያልፋሉ፤ በዚያች በቤተክርስቲያን 15 ዓመት በተጋድሎ ኖረ ከዚያም ወደ አገሩ ተመልሶ በአባቱ ደጅ 15 ዓመት ወድቆ ለመነ:: አባቱ አሸከሮቹን እንዲህ አለ ይህንን ደሃ ምጽዋት ስጡት ልጄ ምናልባት ልክ እንደዚህ ደሃ ሆኖ በሰው አገር እየተንከራተተ ይሆናልና አላቸው:: የአባቱ አሸከሮች ግን የእጅ እጣቢ፤ሽንት ይደፉበት ነበር በላዩ ላይ አጥንት እየወረወሩ ውሾች እንዲጣሉበት ያደርጉ ነበር:: በእንዲህ ያለ ተጋድሎ 15 ዓመት ኖረ፤የእረፍቱ ቀን ጥቅምት 14 ሲደርስ የንጉሱ የቴዎድዮስ ልጅ መሆኑን የደረሰበትን ሁሉ መከራ ጽፎ ይሞታል፤ሊቀብሩት ሲሰበሰቡ ይህችን ጽሁፍ ያገኛሉ:: አባትና እናቱ መሪር ለቅሶ አለቀሱ አገሩ በሙሉ አለቀሰለት ከበድኑ አስገራሚ ተአምራት ተገለጹ ድውያን ሁሉ ተፈወሱ፤በታላቅ ክብርም ቀበሩት፤ +++++++የቅዱሳኑ የአባታችን አቡነ አረጋዊ፡ የጻድቁ መናኝ ገብረ ክርስቶስ እንዲሁም የሐዋርያው ፊሊጶስ በረከታቸው ረድኤታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን ፡፡
Home
New Page
ትምህርተ ሀይማኖት:ምስጢረ ሥላሴ
ምስጢረ ሥጋዌ
ምስጢረ ጥምቀት
የላሊበላ ሕንፃ ቤተክርስቲያን ምስሎች
ነገረ ማርያም
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ፃድቁ መናኝ ገብረ ክርስቶስ
የክርስቶስ ጥልቅ ፍቅር
የመንፈሳዊ ሕይወት ደረጃ
መተግበሪያ (APPS)
Contact us
yilma mezmur
daniel kibret
temhirtoch
megabi eshetu
memhir zebene lemma
memhir miherete ab aseefa
mezmur
tedros yosef
our other site
live tv
read pdf files