ምስጢረ ሥጋዌ
ምስጢረ ሥጋዌ ማለት “ቃል ስጋ ሆነ በእኛም አደረ” በሚለዉ የወንጌል ቃል ላይ የተመሰረተ ታላቅ
የክርስትና ሃይማኖት ምስጢር ነዉ ። ዮሐ. 1 ፤ 14 ። ስለሆነም ምስጢረ ስጋዌ ማለት የእግዚአብሔር
አካላዊ ቃል ወልድ ሰዉን ለማዳን ሲል ሰዉ የሆነበት ፤ ሰዉን ያዳነበት ፤ መለኮትና ትስብእት በተዋህዶ
አንድ የሆኑበት ምስጢር ማለት ነዉ።
ክርስቶስ በቃልነቱ በመለኮቱ ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ከእግዚአብሔርም የተገኘ አምላክ ወልደ አምላክ
እንደሆነ፤ በስጋ ደግሞ ከአዳም ተገኝቷል። እኛን ሰዎችን ለማዳን ከእኛ ጋር ዝምድና መስርቷል። ከቅድስት
ድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ሰዉ በመሆኑና በመወለዱ ከአዳም
ልጆች ጋር ያለዉን ዝምድና በተዋሐደዉ ስጋ አጽንቶታል።ከቅድስት ድንግል ማርያም በመወለዱ
የእግዚአብሔር ልጅ የሰዉ ልጅ ሆኗል፤ እርሷም የእግዚአብሔርን ልጅ ክርስቶስን በመዉለዷ የአምላክ
እናት ሆናለች። ስለዚህ ክርስቶስ ሁለት ልደት እንዳለዉ እናምናለን። ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት
መወለዱ፤ አንድ ልደት፤ ድህረ ዓለም ከእመቤታችን ያለ አባት መወለዱ፤ ሁለት ልደት፤ ወልደ አብ ወልደ
ማርያም በተዋሕዶ ከበረ በማለት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን እንገልጻለን።